ዕድር የሚለው ቃል ብዙ አይነት ፍቺ አለው ይኅውም ፣
ዘየ ወይም ልማድ ይሆናል፣ ለምሳሌ የእገሌ ሀገር ዕድር እንዲህ ነው ሲል ልማዱ ዘየው እንዲህ ነው ማለት ይሆናል ።
ኅብረት፣ አንድንት ማለት ይሆናል ፣ይህንም የመሳስሉ ልዩ ልዩ ትርጉሞች አሉት ግን አሁን በዚህ ዘመን የሚታየው የስራው አፈፃፀም የሚያመለክተው ሁለተኛውን ቁጥር የመሰለ ሆኖ እናገኘዋለን።
ስለዚህ ዕድር ማለት አሁን ለቀብር ጊዜ የሚያገለግል ዉል ፣የቀብሩን ስረዓት የሚመለክት ገንዘብ የሚዋጣበት አገልግሎት ነው። ይህም ማለት አንድ ሰው ኃዘን ሳይደርስበት አስቀድሞ ገንዘብ ያዋጣል የተለያየ ሃሳብም ይለዋወጣል ፣ እንደዚሁ አድርገው የሚያዋጡት ገንዘብ ይህም የሚወስኑት ውሳኔ ማህበሩም በጠቅላላ የሥራውም አፈፃፀም ነው ።
ዕድር መልኩን ለውጦ ነው እንጂ እዝን ከምንለው ጋር በጣም ይመሳስላል እንዲያዉም እርሱን አሻሽሉት መልኩን ለወጡት ለማለት ይቻላል ፣ ምክንያቱም እዝን በዚያው በአደጋው ዕለት የሚያዋጡት ወይም የሚሰጡት ነገር ሲሆን ዕድር ግን አስቀድሞ የተወሰነ ገንዘብ ሲያዋጡ ቆይተው ቦሀላ በሀዘኑ ፣ በችግሩ ጊዜ የሚረዱት ወይም እርዳታ የሚሰጡበት አገልግሎት ነው ።
ምንጭ : ማህበራዊ ኑሮ በኢትዮጵያ( በሊቀ ስልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ)